AMN – የካቲት 23/2017 ዓ.ም
ጀግኖች አባቶቻችን መስዋዕትነት ከፍለው ያስረከቡንን አደራ በአድዋ መንፈስ መድገም ይገባል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ አሳሰቡ፡፡
ኢንጅነር አይሻ መሀመድ “አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል ለ129ኛ ጊዜ እየተከበረ በሚገኘው የአድዋ ድል አከባበር ላይ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ላይ አድዋ የምንዘክረው ታሪክ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ የምናወርሰው ታላቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አድዋ የመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት በዓል መሆኑን ጠቁመው አፍሪካውያን ለነፃነት የሚያደርጉትን ንቅናቄ በማቀጣጠል ለድል እንዳበቃቸው በመግለጽ ፣ ዛሬም በህብረትና በጀግንነት በመነሳሳት ለሀገራችንና ለአፍሪካ ብልፅግና ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባ ጭምር ጠቁመዋል።
አክለውም ጀግኖች አባቶች እና እናቶቻችን በመስዋዕትነት ያስረከቡንን ሀገር አንድነታችንን በማጠናከር እና በዘመኑ የገጠሙኑንን ፈተናዎች በመሻገር ጠንካራ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን እንዲሁም አፍሪካን ለመገንባት መጠቀም ይገባናል ብለዋል::