ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራልን የጎበኙ ሲሆን ይኽም የቅርሱ መጠበቅን ባሕላዊ እና አለምአቀፍ ዋጋ ያመላከተ ነበር። እ.ኤ.አ በ2019 ከተከሰተው የእሳት አደጋ በኋላ የተደረጉ የጥበቃ ሥራዎች ፈረንሳይ ለታሪካዊ ምልክቶቿን ጠብቃ ለመጪ ትውልዶች ለማቆየት ያላትን ፅኑ አቋም የሚያሳዩ ናቸው።
ጉብኝቱ ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ትምሕርት የሰጠ ነው። ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጎንደር ፋሲለደስ እስከ አባጅፋር ጅማ ቤተመንግሥት እና በርካታ ቅርሶች ድረስ አቻ የማይገኝለት የታሪክ እና የባሕል ሀብት እንዳላት ሀገር ኢትዮጵያ ሀገራችን የቅርስ ጥበቃ እና እድሳትን ቅድሚያ የምትሰጥበት በርካታ ፀጋ አላት። ቱሪዝምን ማስፋፋት የጠቅላይ ሚኒስትር ቁልፍ የትኩረት መስክ በመሆን በኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ከአምስቱ ምሰሶዎች አንዱ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል።

ከአለም አቀፍ ምርጥ ተመክሮ በመማር ኢትዮጵያ የባሕል ሀብት ቅርሶቿን የመጠበቅ እና ቀጣይነት ያለው የቱሪዝም ልማት ሥራ ጥረቷን ለማጠናከር እንደሚያስችላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡