AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐረር የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም፣ ለክልሉ ኮሪደር ፕሮጀክቶች በሀገር ውስጥ የተሰሩ ቁሳቁስ የሚያመርተውን የማስ ኢንጂነሪንግ ኢንተርፕራይዝ እና የሌማት ትሩፋት ማሳያ ተመልክተዋል።
ለክልሉ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውን የዳቦ ፋብሪካ ተዘዋውረው መመልከታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።