AMN – መጋቢት 2/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን መመልከታቸውንና መትጋት፣ መሥራት፣ ማየት ከቻልን፣ ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች ብለዋል።
አክለውም ይህ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል።