AMN – ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ተቋሙን ሲመሩ የቆዩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት የኀዘን መግለጫ መልዕክት፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መፅናናትን ተመኝተዋል።
የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን አመራሮች እና ሠራተኞችም በጌታቸው መለስ (ዶ/ር) ኅልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን በመግለጽ ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ መፅናናትን ተመኝተዋል።