AMN-የካቲት 11/2017 ዓ.ም
ዛሬ ምሽት ከራሺያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተገናኝተው
መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ፣ የነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ እና የራሺያ ግንኙነቶችን ለመዳሰስ እና ለመወያየት ጥሩ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።