ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቬይትናም ፕሬዝዳንት ጄነራል ሉዎንግ ኩዎንግ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቬይትናም ፕሬዝዳንት ጄነራል ሉዎንግ ኩዎንግ ጋር ተወያዩ

AMN – ሚያዚያ 8/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቬይትናም ፕሬዝዳንት ጄነራል ሉዎንግ ኩዎንግ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ከብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ትራን ታንህ ማን ጋርም መክረዋል።

ውይይቶቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቬይትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ የሚያደርጉትን ይፋዊ ጉብኝት አካል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በሁለቱም ውይይቶች ስለ ሀገረ መንግሥት ቀጣይነት፣የፖለቲካ ትብብር፣የለውጥ ጥረቶች የተነሱ ሲሆን በብዙ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትስስሮችን እና ትብብሮችን ይበልጥ ለማጠናከር የሚቻልባቸው መንገዶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review