AMN- የካቲት 7 /2017 ዓ. ም.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ዩኤንፋኦ) ዳይሬክተር ጀነራል ኩ ዶንግዩን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በውይይታቸው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ዘላቂነት እና በዘርፉ ለሚያስፈልገው ጽናት ተባብሮ የመሥራትን አስፈላጊነት በማውሳት የኢትዮጵያን ቀጣይ የግብርና ሥራ ጥረቶችን መመልከታቸውን አመላክተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ዩኤንፋኦ) ዳይሬክተር ጀነራል ኩ ዶንግዩን በድጋሚ በማግኘታቸውም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።