ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንጎላ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በጽ/ቤታቸዉ ተቀብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ ጠዋት ከፕሬዝደንት ጁአዎ ማኑኤል ጎንካሌቭ ሎሬንቾ በልዩ መልዕክተኝነት መልዕክት ይዘው የመጡትን የአንጎላ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴቴ አንቶኒዮንን በጽሕፈት ቤታቸዉ መቀበላቸዉን ገልጸዋል፡፡