“ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ኅብረብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት መሠረት ነው” – የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

You are currently viewing “ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ኅብረብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት መሠረት ነው” – የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

AMN – ኅዳር 20/2017 ዓ.ም

ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ኅብረብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት መሠረት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ገለጹ።

ወ/ሮ ቡዜና ይህን ያሉት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተገኝተው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ማጠቃለያ መርሐ-ግብር ላይ የአብሮነት ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበርም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታችንን ይበልጥ በማጎልበት፣ በወል ጉዳዮቻችን ዙሪያ ብሔራዊ መግባባትን እውን ለማድረግ በሚያስችል መልኩ እየተከበረ ይገኛልም ብለዋል።

በታሪካዊቷ በአፋር ሕዝቦች ክልል የበዓል አከባበር ላይ ተገኝተው መልዕክት እንዲያስተላልፉ ለጋበዛቸው ለአፋር ብሔራዊ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ ምስጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review