ጥምቀት ከሃይማኖታዊ በዓልነቱ በተጨማሪ ማህበራዊ እሴቱም ሰፊ እና ጥልቅ ነው-አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing ጥምቀት ከሃይማኖታዊ በዓልነቱ በተጨማሪ ማህበራዊ እሴቱም ሰፊ እና ጥልቅ ነው-አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN-ጥር 10/2017 ዓ.ም

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሙሉ መልዕክታቸው እንደሚከተለው ቀርቦል፦

የጥምቀት በዓል የመገለጥ በዓል ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን በምድር ከተመላለሰባቸው 33 ዓመታት ውስጥ 30 ዓመቱን ሐዋርያትን ሳይጠራ የተለያዩ ስራዎችን የሰራ ሲሆን ከተጠመቀ በኋላ እንዳከናወናቸው በህዝቡ ዘንድ ብዙም የተገለጡ አልነበሩም።

በ30 ዓመቱ በባህረ ዮርዳኖስ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ባሉት ሶስት ዓመታት ከሀጢያት በስተቀር ያሉ መልካም ተግባራትን ሁሉ አከናውኗል ፤ ብዙዎቹም ተግባራቶቹ ለደቀ መዛሙርቱ እና ለህዝቡ የሚታዩ ነበሩ።

ጥምቀት ፈጣሪ በፍጡሩ በቅዱስ ዮሐንስ ፊት ዝቅ ብሎ የተጠመቀበት የትህትና እና የፍቅር በዓል መታሰቢያ ነው ፤ አርአያነቱ ደግሞ ለሁላችንም ነው ፤ አገልጋይነትን መላበስ ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

ከተራ ደግሞ ባህረ ጥምቀቱ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ውሃን ማከማቸት መሰብሰብ ነው::

በአካታቹና በአሰባሳቢው የመደመር መንገድ ህዝባችንን አስተባብሮ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ሌት እና ቀን እየተጋ የሚገኘው ፓርቲያች ለአደባባይ በዓላትም ተጨማሪ ድምቀት የምትሆን ውብ ከተማ እየገነባ ይገኛል።

የከተማችን ትክክለኛ ውበት በግልፅ መታየት ጀምሯል። ጥምቀት ደግሞ ከሀይማኖታዊ በአልነቱ በተጨማሪ ማህበራዊ እሴቱም ሰፊ እና ጥልቅ ነው፡፡

” ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ” የሚለው የአገራችን አባባል ጥምቀት ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ ህፃናት ፣ እናቶች ፣ አባቶች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አቅሙ በፈቀደ መጠን አምሮና ተውቦ ፣ ታቦታቱን አጅቦ በፍቅርና በደስታ የሚያከብሩት ደማቅ በዓል ነው።

በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካሞችን እየደገፍን ፣ የደከሙትን እያበረታታን ፣ ለበዓላትም ተጨማሪ ድምቀት የሆኑትን መሰረተ ልማቶችም በባለቤትነት እየጠበቅን ሊሆን ይገባል።

እንኳን ለከተራ እና ለብርሃነ ጥምቀት በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ ! አደረሰን !

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review