
AMN- ህዳር 12/2017 ዓ.ም
ጽንፈኛው ፋኖ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የፈፀመውን ዘግናኝ እና አጸያፊ ድርጊትን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አወገዘ
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል
ቢሮው ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በሰጡት መግለጫ ሽብርተኛው ሸኔም በኦሮሞ ሕዝብ ላይ አሰቃቂ ግዳያዎችን ፈጽሟል ብለዋል።
የጽንፈኛው ፋኖ እና የአሸባሪው ሸኔ ድርጊት የትኛውንም ሕዝብ የማይወክል እንደሆነም አስታውቋል።
ሸኔም ይሁን ፋኖ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ፈጽመዋልም ብሏል ቢሮው በመግለጫው።
የፋኖ ጽንፈኛ ሐይል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመግታት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ጽንፈኛው ፋኖ ለኦሮሞ ሕዝብና ለብሄር ብሄረሰቦች ያለውን ንቀት ያሳየበት ድርጊትን ፈጽሟልም ብለዋል ቢሮ ሀላፊው በመግለጫቸው።
የሁለቱ የጥፋት ሐይሎች ድርጊት የኦሮሞ እና የአማራን ሕዝብ ለመነጠል የሚያደርጉት እንቅሰቃሴ በመሆኑ ሕዝቡ አሁንም በጋራ መቆም እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
መንግስት የሰላማዊ ዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በጽንፈኞች እና አሸባሪዎች ላይ የሚወስደውን አስፈላጊ እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡
በጽንፈኛ እና አሸባሪዎች ላይ በሚወሰደው እርምጃ ላይ ሕዝባችን አንድነቱን እና አብሮነቱን ጠብቆ ትብብሩን እንዲያጠናክር ቢሮ ሀላፊው ጠይቀዋል።
በዳንኤል መላኩ