ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ባላቸው የህዝብ ብዛትና የማምረት ዕምቅ አቅም በትብብር ከሰሩ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡-ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)

You are currently viewing ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ባላቸው የህዝብ ብዛትና የማምረት ዕምቅ አቅም በትብብር ከሰሩ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡-ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)

AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም

ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ባላቸው የህዝብ ብዛትና የማምረት ዕምቅ አቅም በትብብር ከሰሩ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ የንግድ እኛ ቀጣናዊ ትብብር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ሃገራት ዋና ኃላፊ አምባሳደር ሃሚድ አስጋር የሚመራ ልዑክ ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡

ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገር ሁለንተናዊ ግንኙነት እንዳላቸው የገለጹት ሚኒስትሩ ሁለቱ ሃገራት ባላቸው የህዝብ ብዛትና የማምረት ዕምቅ አቅም በትብብር ከሰሩ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ የጋራ ግንዛቤ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ሃሚዲ ኢትዮጵያ ላሳየችው የውጭ ንግድ ዕድገት አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ የኢትዮጵያ ምርቶች በፓኪስታን ገበያ በስፋት እንዲቀርቡ ለማመቻቸት ቃል መግባታቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥለው ግንቦት ወር ፓኪስታን በአዲስ አበባ ለምታዘጋጀው ኤክስፖም ድጋፍ እንደሚደረግም አስረድተዋል ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review