ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

AMN – ጥር 10/2017 ዓ.ም

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኛውን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ውይይቱም በወቅታዊ የልማት፣ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም ሀገራዊ፣ ክልላዊና የጎንደር ከተማ የቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮረ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review