የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ ከአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በዋነኛነት በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን እና በዲሞክራቲክ ኮንጎ ያለው የሰላም መደፍረስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ በሚቻልበት ሁኔታ እና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም ሁለቱ ባለስልጣናት የአፍሪካ ሕብረት እያደረገ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ላይ መምከራቸውም ተመላክቷል፡፡
ፕሬዝዳንት ታየ አዲሱ የሕብረቱ ተመራጭ ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከአፍሪካ ሕብረት ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡