ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለትንሳዔ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ።
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ እንኳን ለክርስቶስ ትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን፣ ይህ ቅዱስ የበዓለ ትንሳዔ ዕለት የደስታ የፍስሀና የመልካምነት ቀን ነው ብለዋል።
በዓሉን በፍቅር፣ በሰላም እና በመተሳሰብ እናክብር ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው ሲሉም አክለዋል።