ፖርቹጋል የኔሽንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነች

You are currently viewing ፖርቹጋል የኔሽንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነች

ፖርቹጋል ስፔንን በማሸነፍ የ2024/25 የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆናለች።

ዛሬ ምሽት በአሊያንዝ አሬና ስፔንን ከፖርቹጋል ያገናኘው የፍጻሜ ጨዋታ በፖርቹጋል አሸናፊነት ተጠናቋል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛው 90 ደቂቃ እንዲሁም በተጨማሪ 30 ደቂቃ 2 ለ 2 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል።

በጨዋታው የፖርቹጋልን ግቦች ኑኖ ሜንዴዝ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሲያስቆጥሩ የስፔንን ግቦች ዙቢሜንዲና ኦያርዛባል ከመረብ አሳርፈዋል።

በመለያ ምት ፖርቹጋል 5 ለ 3 በማሸነፍ የ2024/25 የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫ ባለቤት ሆናለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review