የአዲስ አበባ ትራፊክ ደንብ ቁጥጥር እና ፓርኪንግ አስተዳደር ሥርዓት ከማንዋል ወደ ዲጂታል መሸጋገሩ ተገለፀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ትራፊክ ደንብ ቁጥጥር እና ፓርኪንግ አስተዳደር ሥርዓት ከማንዋል ወደ ዲጂታል መሸጋገሩ ተገለፀ

AMN – ታኅሣሥ 24/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የከተማዋን የትራፊክ ቁጥጥር እና ፓርኪንግ አስተዳደር ሥርዓት ከማንዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግር ሶፍትዌር አበልፅጎ ለትግበራ ማብቃቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ባለሥልጣኑ ኢንፍራ ቴክ ከተባለ ሶፍትዌር አበልፃጊ ተቋም ጋር በመሆን በከተማዋ የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች የቅጣት ክፍያቸውን እንዲሁም የፓርኪንግ አገልግሎት ክፍያቸውን ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የሚከፍሉበትን አሠራር አስጀምረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደተናገሩት ቴክኖሎጂው በፓድ ሲካሄድ የነበረውን የትራፊክ ቅጣት እና የፓርኪንግ አገልግሎት ክፍያን ወደ ዲጂታል በመቀየሩ የተገልጋይን እንግልት የሚያስቀር በየዓመቱ ለፓድ ህትመት የሚወጣን ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚያስቀር ነው፡፡

በመርሓ ግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ እና የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር ( ዶ/ር ) ፣ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚንስትር ዴኤታ በርሖ ሃሰን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ተገኝተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review