የዜጎችን ኑሮ የሚያሻሽሉ ሰው ተኮር የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል- አቶ አደም ፋራህ

  • Post category:ልማት

AMN-ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም

የዜጎችን ኑሮ የሚያሻሽሉ ሰው ተኮር የሆኑ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

አቶ አደም በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የሌማት ትሩፋት ሥራ አካል የሆነውን የወተት ላሞች እርባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሰው ተኮር ሥራ ሆኖ የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በጉብኝቱ በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ሃላፊና የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባል ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) እና የትራስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review