“ብስክሌት በአዲስ ” የብስክሌት ፌስቲቫል ተካሄደ

AMN – ታኅሣሥ 27/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ከነፍ ኮሙኒኬሽን እና ኤቨንትስ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የመጀመሪያው ወርሃዊ የብስክሌት ፌስቲቫል ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ያብባል አዲስ እንደገለጹት፣ የከተማ አስተዳደሩ በኮሪደር ልማቱ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ልማቶች ውስጥ አንዱ የብስክሌት መንገድ ነው፡፡

ፌስቲቫሉ የተዘጋጀው በዋነኝነት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በፌስቲቫሉ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም የሞተር አልባ ትራንስፖርት መጠቀም ከተማዋን ከተለያዩ በካይ ጋዞች ከመከላከል ባለፈ አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የብስክሌት አገልግሎት አንዱ የትራንስፖርት አማራጭ ሆኖ እንዲቀጥል በትኩረት እንደሚሰራም በፌስቲቫሉ ላይ ተመላክቷል፡፡

በፊርደውስ አብዱልሐኪም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review