ማህበራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተሰራ ያለው የመረዳዳት ተግባር ባህል እየሆነ መጥቷል፡-አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing ማህበራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተሰራ ያለው የመረዳዳት ተግባር ባህል እየሆነ መጥቷል፡-አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም

ማህበራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተሰራ ያለው የመረዳዳት ተግባር ባህል እየሆነ መምጣቱን በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ።

አቶ ሞገስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ማዕድ አጋርተዋል።

በዓላት በመጡ ቁጥር ጓዳቸው ለሚያጥር ‘ማዕዳቸው ለሚሳሳ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ የማካፈልና የመረዳዳት ባህል እየጎለበተ መምጣቱን አቶ ሞገስ ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ማህበራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ& በሰው ተኮር ስራዎቹ የዜጎችን ችግር የሚያቃልሉ አንዱ የአንዱን ችግር እንዲጋራና እንዲረዳዳ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ ነው ብለዋል።

እነዚህ ስራዎች ባህል ሆነው እንዲዘልቁ እና ለትውልድ እንዲሻገሩ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ሞገስ የከተማዋ ነዋሪም ይህንን እሴት ሊያጎለብተው ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የገና በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀው የማዕድ ማጋራት ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ያሉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲሱ ሻንቆ ድጋፉ ሁሉም በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፍ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ማዕድ ማጋራቱ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፣ዝቅተኛ ደመወዝ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች ፣ የፖሊስ አባላት ፣በልማት ከክፍለ ከተማው ለተነሱና በተለያዩ አካባቢዎች ለሚኖሩ የልማት ተነሺዎች ነው የተጋራው።

በዓሉን ምክንያት በማድረግም በአዋሽ ባንክ ድጋፍ የተገነቡ 27 ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ተላልፈዋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review