
AMN – ታኀሣሥ 28/2017 ዓ.ም
የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ኃላፊው በመልዕክታቸው፣ “ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ፣ ሰው የሆነው እና የተወለደው የሰው ልጆችን ሁሉ ለማዳን ነው” ብለዋል፡፡ “ምንም ነገር የማይሳነው ፈጣሪ በከብቶች በረት መወለዱ አንድም ትህትናን ለማስተማር እንዲሁም ፍቅሩን ሊያሳየን ጭምር ነው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
“የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስናከብርም የእኛን እርዳታ የሚሹ ወገኖቻችን በመርዳት ፣ በመደገፍ ፣ ፍቅራችንን በመግለፅ በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ህይወት ትርጉም ባለው መልኩ ለማሻሻል እያደረገ ባለው ጥረት ተጨባጭ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በሰው ተኮር ፕሮግራሞችም የከተማዋ ነዋሪዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በዓሉን በመተሳሰብ እና በመረዳዳት በአብሮነት እንድናከብር ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡