
AMN – ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም
ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ልህቀት ማዕከል በ2ኛ ዙር የስልጠና መርሃ ግብሩ በተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያው ችግር ውስጥ የሚገኙ 500 የሚደርሱ ሴቶችን በነገው ዕለት ይቀበላል ፡፡
ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የአዲስ ሰልጣኖችን አቀባበል አስመልክቶም በግቢው ውስጥ የአቀባበል ስነ ስርአት ይከናወናል፡፡
ማዕከሉ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያው ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን በማብቃት በከተማዋ እንቅስቃሴ እና ልማት ውስጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ እያደረገ ይገኛል፡፡
ማዕከሉ በ1ኛ ዙር የተቀበላቸውን ከ300 በላይ ሰልጣኞች በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ በማስመረቅ ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉም ይታወቃል ፡፡