AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም
የገቢዎች ሚኒስቴር በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከ451 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ገቢው ከሃገር ውስጥ ታክስ እንዲሁም ከጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ የተገኘ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በግምገማው ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ባለፉት ስድስት ወራት በሐገር ውስጥ ታክስ 247 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከውጭ ንግድ ቀረጥ እና ታክስ 203 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር መሰንሰቡን ገልጸዋል፡፡

በድምሩ ከሃገር ውስጥ ታክስ እና ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ 451 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወይም የዕቅዱን 101 በመቶ መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል፡፡
የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ106 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡
የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ከማሻሻል ባለፈ ጠንካራ ሕግ የማስከበር ሥራዎች መከናወናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ ከሚኒስትሯ በተጨማሪ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፣ ምክትል ኮሚሽነሮች እና ሌሎች አካላት መገኘታቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡