ተቋማት የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶችን በማጠናከር ባህል ሊያደርጉት ይገባል፦አቶ ዳኘው ገብሩ

You are currently viewing ተቋማት የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶችን በማጠናከር ባህል ሊያደርጉት ይገባል፦አቶ ዳኘው ገብሩ

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

ተቋማት የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶችን በማጠናከር ባህል ሊያደርጉት እንደሚገባ የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኘው ገብሩ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል እና ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከ800ሺ ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፍ መርሀግብሩ ላይ የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኘው ገብሩ እንደገለፁት ተቋማት ኢትጵያዊ የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶችን ሲተገብሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሽንቁሮችን በመድፈን ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የመደጋገፍ እና የመረዳዳት እሴትን ማጎልበት እንደሚገባም አመልክተዋል።በዚህም ባለስልጣኑ ማህበራዊ ሀላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዳይሬክተር ሂርጳሳ ጫላ (ዶ/ር) በበኩላቸው ማዕከሉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያው ችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶች መጠጊያ፣ ተስፋና ክህሎት አግኝተው በውስጣቸው ያለውን መክሊት የሚያዳብሩበት መሆኑን ገልፀው ባለስልጣኑ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የሜቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል መስራችና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ያሉብንን ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ለመሻገር አንዱ የሌላኛውን ሸክም ሊሸከም ይገባል ብለዋል፡፡

መሰል መረዳዳትና መደጋገፍም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመልክተዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review