ዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ የምርምር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም

15ኛው ዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ የምርምር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡

ጉባኤው ”የምልክት ቋንቋን መጠቀም ለመፃዒው ዘመን፤ መፃኢው ዘመንን ምልክት ቋንቋን በመጠቀም” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል።

በጉባዔው ጥናታዊ ፅሁፎችና ምክረ-ሃሳቦች እንደሚቀርቡበትም እንዲሁ።

ጉባዔው በዘርፉ ለሚከናወኑ ተግባራት ስኬታማነት እገዛ የሚያደርጉ ጠቃሚ የፖሊሲ ግብዓቶችን ለመሠብሠብና ልምድ ለመቅሰም አላማ ያደረገ እንደሆነም ተጠቅሷል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሔራዊ መስማት ከተሳናቸው ማህበር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁትም ተገልጿል።

በጉባዔው ከተለያዩ የአለም አገራትና ተቋማት የተውጣጡ ከ600 በላይ ታዳሚዎች በአካልና በበይነ መረብ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review