የአዲስ አበባ የልማት ስራዎች ለቱሪስት ፍሰት ጉልህ አበርክቶ እየተጫወቱ ነው፡- የቱሪዝም ሚኒስቴር

You are currently viewing የአዲስ አበባ የልማት ስራዎች ለቱሪስት ፍሰት ጉልህ አበርክቶ እየተጫወቱ ነው፡- የቱሪዝም ሚኒስቴር

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ባለፉት አመታት የተሰሩ የልማት ስራዎች ለቱሪስቶች ፍሰት ትልቅ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበ፣ አዲስ አበባ በሆቴሎች፣ በመንገዶች እና መሰል መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ባከናወነቻቸው ስራዎች ከተማዋን የቱሪዝም ኮንፈረንስ ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል፡፡

መዲናዋ ከአለም አቀፍ ጎብኝዎች በተጨማሪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአራቱም ማዕዘን መጥቶ ሊጎበኛት የሚመኛት ሆናለች ያሉት ሚኒስትር ዴዔታዉ ከውጭ ቱሪስቶች በተጨማሪ በሀገር ውስጥ ቱሪስቶች መዳረሻ እንድትሆን የቱሪዝም ሚኒስቴር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ጥር ወርን ለቱሪዝም ዘርፉ ለመጠቀም ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ዶክተር እንደገና አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ የአደባባይ በዓላት ጎልተው እንዲወጡ ለማስቻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review