AMN – ጥር 8/2017 ዓ.ም
የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን እና የቱሪስት መስህብነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ተባብረን በጋራ እንስራ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ማምሻውን የጥምቀት በዓልን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
የጥምቀት በዓል የተለመደውን ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ ከሃይማኖቱ አባቶች ጋር ተወያይተናል ያሉት ከንቲባ አዳነች ሁላችንም በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን እና የቱሪስት መስህብነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ተባብረን በጋራ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡