AMN – ጥር 10/2017 ዓ.ም
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉና የጎንደር ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።