ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ሥራቸው ስደተኞችን ማስወጣት መሆኑን ገለጹ

You are currently viewing ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ሥራቸው ስደተኞችን ማስወጣት መሆኑን ገለጹ

AMN-ጥር 12/2017 ዓ.ም

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮአቸውን እንደተረከቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ስደተኞችን ማስወጣት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በአስተዳደር ዘመናቸው ቅድሚያ ለመፈጸም ቃል የገቡዋቸውን ቁልፍ ጉዳዮች እንደሚፈጽሙ አረጋግጠዋል፡፡

በዚህም ዶናልድ ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ዋዜማ በሺዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ስደተኞችን በተመለከተ ጠንከር ያለ ገደብ እንደሚጥሉ ተናግረዋል፡፡

በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት በገቡት ቃል መሠረትም በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ስደተኞችን እንደሚያስወጡ ገልጸዋል፡፡

ትራምፕ በፈረንጆቹ ጥር 6 ቀን 2021 በካፒቶል ከተፈፀመ ጥቃት ጋር በተያያዘ ክስ ለተመሰረተባቸው እና ለተፈረደባቸው ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ይቅርታ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

በቅርብ ሳምንታት፣ ትራምፕ ግሪንላንድን እና የፓናማ ቦይን የመቆጣጠር እና ካናዳን ወደ አሜሪካ ግዛት ስለመቀላቀል ያነሱት ሀሳብ የአሜሪካን የውጭ አጋሮች ግራ ማጋባቱ አይዘነጋም።

አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችን በሽብር ቡድን መለየትን ጨምሮ በአሜሪካ እና በሜክሲኮ ድንበር ድንገተኛ አደጋ በማወጅ፣ ሜክሲኮአዊ ያልሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች የፍርድ ቤት ውሳኔ እስኪያገኙ በሜክሲኮ እንዲቆዩ የሚያስገድደው ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲደረግ እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡

በአሜሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያግድ ህግ የተጣለበት ቲክቶክ፣ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ ያደረጉት ዶናልድ ትራምፕ፣ በዓለ ሲመታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ለ90 ቀናት እንዲቆይ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ቀናቸው ሌሎች በርካታ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፉም ይጠበቃል።

All reactions:

194194

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review