በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥም የጡንቻ ህመም መንስኤና መከላከያው

You are currently viewing በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥም የጡንቻ ህመም መንስኤና መከላከያው
  • Post category:ጤና

የጤና መረጃ

በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥም የጡንቻ ህመም መንስኤና መከላከያው

በእርግዝና ወቅት ከሚከሰቱ የተለመዱ የበሽታ አይነቶች መካካል አንዱ የጡንቻ መኮማተር እንደሆነ በጤና ባለሙያዎች ይነገራል፡፡

መንስኤዎች፡-

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የጡንቻ ህመም መንስኤው በዋነኝነት የእናትየዋ የአካል ክፍል እያደገ የመጣውን ፅንስ ለመሸከም እንዲችል በሚያደርጋቸው የፊዚዮሎጂ እና የሰውነት ለውጦች አማከኝነት እንደሆነ የማዘርስ ሄልዝ የተሰኘው የጤና መረጃዎች ያመላክታል፡፡

ለውጡም በጡንቻዎች እና በመገጣጠሚያዎች ላይ ተጨማሪ ጫና እንዲፈጠር የሚያደርገውን የሆርሞን መለዋወጥ፣ የክብደት መጨመር እና ሌሎችም ክስተቶች እንደሚያካትት ተመላክቷል፡፡

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የጡንቻ ህመም በአብዛኛው ከባድ እንቅስቃሴ ያለባቸውን ስራዎች በሚሰሩ እናቶች ላይ በይበልጥ የሚከሰት ህመም ቢሆንም አንዳንዴ ግን በቂ የሆነ ፈሳሽ ካለመውሰድጋር በተያያዘም ሊከሰት እንደሚችል መረጃው ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች በተለይም ካልስየም፣ማግኒዥየምና ፖታስየም እጥረት ሲያጋጥም ህመሙ ሊከሰት እንደሚችልም የጤና ባለሙያዎች ይጠቁማሉ፡፡

መከላከያው/ህክምናው፡-

በአብዛኛው ከባድ እንቅስቃሴዎችን መቀነስ፣
ፈሳሽ በደንብ መውሰድ፣
በቀን ውስጥ ውሃን አብዝቶ መጠጣት፣
አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን በተለይም ካልስየምና ማግኒዥየም የሚገኙባቸውን ምግቦች ማለትም እንደ ወተትና የወተት ተዋጽኦዎች ያሉባቸውን ምግቦች መጠቀም አማራጭ የህክምና ዘዴ እንደሆነ የጤና መረጃው ያመላክታል፡፡

እንዲሁም አካሄድን፣ አቀማመጥንና አተኛኘትን ማስተካከል እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
ሌላው በእርግዝና ወቅት ከፍተኛ ተረከዝና ሶል ያላቸውን ጫማዎች ከመጫመት መቆጠብና ጠፍጣፋ ተረከዝ ያላቸውን ጫማዎች መጠቀም፣ በሚቀመጡበት ጊዜ ተስተካክሎ መቀመጥ፣ወገብ ላይ ድጋፍ እንዲኖር ማድረግ፣ ሲተኙ በተቻለ መጠን በጎን መተኛትና በእግሮች መካከል የትራስ ድጋፍ መጠቀም አስፋላጊ እንደሆነም ነው የጤና ባለሙያዎች የሚመክሩት፡፡

ከእርግዝና በፊት የታወቀ የጡንቻ መኮማተርና ሌሎች ህመሞች ካሉና ለእነዚህ ህመሞች የሚወሰዱ መድሃኒቶች ካሉ ከእርግዝና ጋር ተስማሚ በሆኑ መድሃኒቶች መቀየር እንደሚያስፈልግም የጤና መረጃው ይመክራል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review