የሌማት ትሩፋት እና የስራ እድል ፈጠራ በከተማ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተሰሩ ያሉ ዘርፎች ናቸው-፡ አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing የሌማት ትሩፋት እና የስራ እድል ፈጠራ በከተማ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተሰሩ ያሉ ዘርፎች ናቸው-፡ አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN – ጥር 13/2017 ዓ.ም

የሌማት ትሩፋት እና የስራ እድል ፈጠራ እንደሀገርም ሆነ እንደከተማ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተሰሩ ያሉ ዘርፎች መሆናቸውን የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ባለፉት ሁለት ወራት በሌማት ትሩፋትና በስራ እድል ፈጠራ በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት እንደከተማ በትኩረትም በትጋትም እየተሰራባቸው ያሉ መስኮች መሆናቸውን አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡

ዘርፉ የጋራ ስራ በመሆኑ በቅንጅት እና በትኩረት ሊመራ ይገባልም ብለዋል።

ባለፉት ሁለት ወራት በነበረው የሌማት ትሩፋት እና የስራ እድል ፈጠራ ላይ የተገኙ ለውጦችን ማስቀጠል እንደሚገባ ያብራሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ፣ ለድክመቶቹም ኃላፊነት መውሰድና ለሚቀጥለው የተሻለ ስራ ለመስራት መትጋት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በፅዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review