በመዲናዋ ከ50 ቢልዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ቋሚ ንብረቶች በዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ስርዓት ተመዝግበዋል፡-የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን

You are currently viewing በመዲናዋ ከ50 ቢልዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ቋሚ ንብረቶች በዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ስርዓት ተመዝግበዋል፡-የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን

AMN – ጥር 14/2017 ዓ.ም

በመዲናዋ ከ50 ቢልዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ቋሚ ንብረቶች በዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ስርዓት መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ከ50 ቢልዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ቋሚ ንብረቶችን መመዝገቡን የንብረት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፀሐይ መንግስቱ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

የንብረት አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን ከኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀት 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሶፍትዌር በማልማት ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።

የቋሚ ንብረት ምዝገባ ስራው በ491 የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት መከናወኑን የገለጹት ም/ስራ አስኪያጇ ከ66 ሺህ በላይ የንብረት ተጠቃሚዎች እጅ ላይ 464 ሺህ በላይ ቁሚ ንብረቶችን መመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

የንብረት አስተዳደር ስርዓትን ማዘመን የስማርት ሲቲ አንድ አካል እንደሆነ የገለጹት ም/ስራ አስኪያጇ የከተማ አስተዳደሩን የንብረት አስተዳደር ስርዓት ማዘመን በመንግስት ንብረት ላይ የሚፈጸሙ ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ውጤታማ የመንግስት ንብረት አያያዝና አጠቃቀም ስርዓትን ለማስፈን ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የቋሚ ንብረት ምዝገባ ያጠናቀቁ ተቋማት 3 መሆናቸውን እና በተመረጡ 17 ተቋማት በንብረት ገቢና ወጪ ላይ ለመንግስት ሰራተኛው በሙከራ ደረጃ የኦን ላይን አገልግሎት የሚጀመር መሆኑን አመላክተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ሶፍትዌሩን በውጤታማነት መተግበር የሚቻል መሆኑን የተረጋገጠ በመሆኑ የፌደራል ተቋማትና ክልሎች ተሞክሮውን በመውሰድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review