ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ በኢኮኖሚ ጉዞዋ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች:- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

You are currently viewing ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ በኢኮኖሚ ጉዞዋ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች:- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

AMN- ጥር 14/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ በኢኮኖሚ ጉዞዋ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ እና የጃፓን የንግድና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይህም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ሴክተር በርካታ እድሎችን ማቅረቡን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት በወጪ ንግድ 3 ነጥብ 28 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን እና በዚህም አስደናቂ አፈጻጸም መመዝገቡን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ጃፓን በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሚታወቁ በርካታ የትብብር እድሎችን የፈጠረ የረጅም ጊዜ ትብብር ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በሁለቱ ሃገራት መካከል በተለይም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢነርጂ እና በቴክኖሎጂ ያለው ሰፊ የኢኮኖሚ ትስስር በመጠቀም የላቀ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በፈረንጆቹ 2023 ኢትዮጵያ ወደ ጃፓን 114 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ሸቀጦችን የላከች ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ሰሊጥ እና አበባን አስከትሎ ቡና 79 በመቶውን ድርሻ ይዟል።

በዚሁ ዓመት ከጃፓን ወደ ኢትዮጵያ 375 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ምርት የገባ ሲሆን፣ ተሽከርካሪዎች ቀዳሚውን ድርሻ መያዛቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review