AMN-ጥር 15/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስጀመሩት እና 5 ሚሊዮን ኮደሮችን ለማፍራት በታቀደው መሰረት ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ የሚገኙ ባለሙያዎች የአምስት ሚልዮን ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረጉን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።
በዛሬው ዕለትም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተገኙበት ከሁለት እስከ አራት ኮርስ የወሰዱ 180 ሰራተኞቹን አስመርቋል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መንግስት ያለማውን ሃገሪቱን ወደ ዲጂታል የማሸጋገር ውጥን ሰልጣኞች እራሳቸውን አብቅተው በዓለም ተወዳዳሪ ሃገር ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ማሳሰባቸውን የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል፡፡