AMN-ጥር 15/2017 ዓ.ም
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ዋና ዕምባ ጠባቂ፣ ምክትል ዕምባ ጠባቂ እና የዘርፍ እምባ ጠባቂ ሹመትን በሙሉ ድምዕ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
በጉባኤውም እጩ ዕንባ ጠባቂዎቹ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ነጻ መሆናቸውን፣ የትምህርት ዝግጅት፣ ታታሪነት፣ ስነ-ምግባርና ሌሎች መስፈርቶችን በማሟላት የተመረጡ መሆኑም መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
በዚህም ወይዘሮ ስመኝ ውቤ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ዋና ዕምባ ጠባቂ፣ የኔነህ ስመኝ(ዶ/ር) ምክትል ዕምባ ጠባቂ እንዲሁም አቶ አባይነህ አዴቶ የዘርፍ እምባ ጠባቂ ሆነው የተሾሙ ሲሆን ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።