መንግስት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing መንግስት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-ጥር 18 / 2017 ዓ.ም

መንግስት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ እንዲሁም የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተፈጥሮ ሀብት በታደለችው ታሪካዊቷ ጅማ ከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ እና የታሪካዊዉን የአባጅፋር ቤተ መንግስት እድሳት ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ ጉብኝታቸውን አስመልክተው ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ መንግስት የቅርሶችን እድሳት እና የኮሪደር ልማት ስራን በመዲናዋ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም በመጀመር ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ እንዲሁም የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

እንግዳ ተቀባይና ሰላም ወዳዱን የጅማ ከተማ እና የአካባቢውን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

“ወደር በማይገኝለት ተሳትፏቸሁ ይህ ራዕይ እውን እንዲሆን በማስቻላችሁ እና ላሳያችሁን ፍቅር ታላቅ ምስጋና ይገባቹሃል” ሲሉም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review