ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው

You are currently viewing ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው

AMN – ጥር 19/2017 ዓ.ም

ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት፣የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የልማት አጋሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማህማ፣ የጊኒ ቢሳው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ እና የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ በስብሰባው ከተገኙ የሀገራት መሪዎች መካከል ይገኙበታል።

በኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሚመራው ስብሰባ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።

ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ በተለይም በህብረቱ ዘላቂ ፋይናንስ እና የስራ መዋቅር ማሻሻያ እንዲሁም ህብረቱ ለአህጉራዊ ፈተናዎች መፍትሄ በመስጠት ግቦቹን ማሳካት የሚችልበት አቅም መገንባት ላይ ያተኮረ ነው።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እ.አ.አ በየካቲት ወር 2024 የአፍሪካ ህብረት የተቋማዊ ማሻሻያ ስራ እንዲመሩ መመረጣቸው እንደሚታወስ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review