ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ከፊጋ – ወደ ሳፋሪ በሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ይሆናሉ

You are currently viewing ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ከፊጋ – ወደ ሳፋሪ በሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ይሆናሉ

AMN-ጥር 19/2017 ዓ.ም

ከነገ ጥር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ – ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2ኛው ዙር ከሚለሙት የኮሪደር መስመሮች መካከል የሰሚት- ጎሮ መንገድ አንደኛው መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ከዚሁ ልማት ጋር በተያያዘ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሲ ኤም ሲ- ፔፕሲ – ጎሮ – መንገድ ልዩ ቦታው ሳፋሪ መብራት አካባቢ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት አጠገብ የመንገድ ቆረጣ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ከነገ ጥር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ – ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በማኅበራዊ ትስስር ገፁ መልዕክት አስተላልፏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review