AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም
ባለፉት 6 ወራት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመት የመንግስትን መብትና ጥቅም ማስከበር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ::
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀሙን በቢሾፍቱ እየገመገመ ነዉ።
ቢሮው ለአስተዳደሩ የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪና ተወካይ ሆኖ እንዲሠራ በአዋጅ ኃላፊነት እንደተሰጠው ይታወቃል::
በዚህም ባለፉት 6 ወራት በፍትሐ ብሔር ከቀረቡ 4 ሺህ 741 የክስ መዝገቦች ውስጥ 1 ሺህ 895 መዝገቦችን ዉሳኔ እንዲያገኙ አድርጓል ፡፡
ከነዚህ ውስጥም 1 ሺህ 766 መዝገቦች ዉሳኔ እንዲያገኙ በማድረግ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመት የአስተዳደሩን መብትና ጥቅም ማስከበር መቻሉ ተገልጿል::
ቢሮው በወንጀል ጉዳዮች ከቀረቡ 7 ሺህ 852 የምርመራ መዝገቦች ሁሉም ዉሳኔ እንዲያገኙ ማድረጉ ተመላክቷል::
የነዋሪውንና የአስፈጻሚ አካላትን ንቃት ህግ ለማስደግ በተከናወኑ ተግባራት አስተዳደሩ የጀመረውን የተቌማት ሪፎርም እንዲሳካ ሚናው የጎላ እንደነበር በመድረኩ ተገልጿል::
በአንዋር አህመድ