የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሓቅ አብዱልቃዲር፡-
*
✓ከዚህ ቀደም የጦርነት ቀጠና ተደርጐ ይወሰድ የነበረው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በተሰራው ሰላምን የማፅናት ስራ አሁን በልማት የሚታወቅ ክልል ሆኗል፡፡
✓ በሁሉም ቀበሌ እና ወረዳዎች ወጣቶች በሚያከናውኑት የእርሻ ስራ ሞዴል አርሶ አደሮች ተብለው እየተሸለሙ ነው፡፡
✓በክልልሉ በይበልጥ ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ ነው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ፡-

**
✓ብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም ዜጎች እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ፓርቲ በመሆኑ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ሰፊ ሥራ ሰርቷል፡፡
✓እስረኞችን ከመፍታት፣ ከሀገር ለቀው የተሰደዱትን ወደ ሀገር ከመመለስ ጀምሮ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፡፡
✓የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ትጥቅ አንግበው ጫካ ከገባው ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ድርድር በማድረግ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ አድርጔል፡፡
✓ልዩነቶችን እንደ ጌጥ እና እንደ ዉበት በመውሰድ ለሰላም ተግቶ መስራት ያስፈልጋል።