በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ተገለፀ

You are currently viewing በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ተገለፀ

AMN- ጥር 21/2017

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተስፋ ሰጪ ተግባራትን እያከናወነ ስለመሆኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመለከተ።

የኢትዮጽያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ 3 አመት ስትራቴጅክ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ስጭ መሆናቸውን እና ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተመርጠው የሚመጡበት ሁኔታ ጥሩ የዴሞክራሲ ልምምድ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሂደቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ቀሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገራዊ ምክክሩን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው በቀጣይ ወደ ውይይቱ መግባት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ሚዲያዎች የኤዲቶሪያል ፖሊሲያቸውን ጠብቀው በቀጣይ ለሚኖረው ሂደት ገንቢ የሆነ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባ በመርሃ ግብሩ ተጠቁሟል።

የኮሚሽኑ ስትራቴጅክ እቅድ አፈፃፀም የመነሻ ሪፖርት በኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በሪፖርቱ ከቀርቡት ጉዳዮች መካከል የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን እንዲሁም ሌሎች መሠል የማህበረሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ በሃገራዊ ምክክር ሂደቱ ከፍ ማለት እንዳለበትና ለዚህም ዝቅተኛው የሴቶች ተሳትፎ 30%፣ የአካል ጉዳተኞች ደግሞ 5% ሲሆን፣ ይህንንም በተቻለ መጠን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለመከወን ግብ ተጥሎ የተሰራ ሲሆን፣ በእስካሁኑ አፈፃፀም የተሻለ ውጤት መመዝገቡን በሪፖርቱ ቀርቧል።

በቀሪ ሁለት ክልሎች (አማራ እና ትግራይ ) እንዲሁም ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደቱ ይሳካ ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስቻይ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ ዋና ኮሚሽነሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review