AMN- ጥር 23/2017
የደቡብ አፍሪካው አፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ (ኤ ኤን ሲ) ፖርቲ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኖጦሉ ኪይቬት አዲስ አበባ ገቡ።
ኖጦሉ ኪይቬት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት የደቡብ አፍሪካው አፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ (ኤ ኤን ሲ) ፖርቲ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኖጦሉ ኪይቬት ወደ ምድረ ቀደምት የሆነችው ኢትዮጵያ በሰላም መጡ ብለዋል::