AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም
በረራ እና ከአደጋው ጋር የተያያዙ አጠቃላይ መረጃዎችን የሚሰጠው ጥቁር ሳጥን መገኘቱ ተገልጿል፡፡
በቀጣይ 30 ቀናት ውስጥ የመጀመሪያ ዙር መረጃ ይፋ ይደረጋልም ተብሏል፡፡
በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ ከሄሊኮፕተር ጋር የተጋጨው አውሮፕላን ለ67 ሰዎች ህልፈት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የዚህ ዓይነቱ የአውሮፕላን አደጋ በአሜሪካ ሲያጋጥም ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል፡፡