AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገልጿል።
በግዛቱ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ20 መንገደኞች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል።
ሚኒስቴሩ ለደቡብ ሱዳን ህዝብ እና መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።
በዚህ ከባድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ደቡብ ሱዳን መንግሥት እና ሕዝብ ጎን በመሆን ያለውን አጋርነትም ገልጿል።