ዶክተር ዲማ ነጎ የኩባ ፖርላማ ልዑካንን ተቀብለው አነጋገሩ

You are currently viewing ዶክተር ዲማ ነጎ የኩባ ፖርላማ ልዑካንን ተቀብለው አነጋገሩ

AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም

በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነጎ (ዶ/ር) የኩባ ፖርላማ ልዑካንን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዶክተር ዲማ ነጎ ኢትዮጵያ ከኩባ ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

በኩባና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የህዝብ ለህዝብና ፓርላሜንታዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንሰራለን ብለዋል።

የኩባ ፓርላማ ከሌሎች አገራት ፓርላማ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያደርገውን ጥረት ኢትዮጵያ እንደምትደግፍ ዶክተር ዲማ አመላክተዋል።

ሁለቱ ሀገራት በጤና፣ በማህበራዊና በወታደራዊ ዘርፎች ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ትብብርና ግንኙነት እንዳላቸውም ገልፀዋል።

ኩባ በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ በርካታ ባለሙያዎች በማሰልጠን አጋርነቷን አሳይታለች ብለዋል።

ኩባ ከኢትዮጽያ ጋር ያላትን የረዥም ዓመታት አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል የኩባ ፓርላማ ልዑክ መሪ ዩዲ መርሴዲስ ሮድርጌዝ ገልጸዋል።

ሁለቱ አገራት ያላቸውን ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ግንኙነት አጠናክሮ ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎትም ልዑካኑ መግለፃቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review