የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝደንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር አንኳር ነጥቦች፡-

You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝደንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር አንኳር ነጥቦች፡-

V👉በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ታሪክ በጣም አጭር እና 60 ዓመት ያልሞላው ታሪክ ያለው ነው

👉አንድ ፓርቲ ለውጥ መፍጠር ብቻ ሳይሆን ለውጥ ለመምራት የሚያስችል ብቃት እስካልፈጠረ ድረስ የተሟላ የፓርቲ ህልውና አይኖረውም

👉ለውጥ መፍጠር ማለት ስላለው ችግር፤ ድካም እና ወድቀት አብዝቶ መናገር ብቻ ሳይሆን መፍትሔ ማፍለቅ ይጠይቃል

👉ብልጽግና ሊያፈርስ የሚፈልገው በርካታ ኋላ ቀር አሰራሮች እና ልምምዶች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡ ነገር ግን ሊያፈርስ የሚፈልገውን ነገር ማፍረስ ብቻ ሳይሆን አልቆ መገንባትን አስቀድሞ የሚያስብ ነው

👉የአንድ ፓርቲ አስኳሉ ሃሳብ ነው፤ የደረጀ ሃሳብ የሌለው ፖለቲካ ፓርቲ የፈለገውን ማፍረስና ለውጥ መፍጠር ቢችልም ለውጥ ለመምራትና የሚያልመውን ለመትከለ ይቸገራል፡፡

👉ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ሀገር በቀል የሆነ እሳቤ ነድፎ የመጣ ፓርቲ ነው

👉ብልጽግና ለኢትዮጵያ ፍቱን መድሃኒት መደመር ነው ብሎ ሃሳብ ይዞ ሲመጣ ላለፉት 6 ዓመታት አሁንም ከሳሽ እንጂ አማራጭ ሃሳብ ይዞ የመጣ ግለሰብ ፣ ቡድን እና ፓርቲ አላየንም

All reactions:

189Tsehhay Habte and 188 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review