AMN – ጥር 23/2017 ዓ.ም
በአፍሪካ ግዙፉ ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ሃሳብ ሲያካሂድ የተርኪዬው ገዢ ኤኬ ፓርቲ እና የራሺያው ገዢ ፓርቲ የራሽያ አንድነት ፓርቲ ተወካዮችም ታድመውበታል፡፡
የተርኪዬው ኤኬ ፓርቲ ምክትል ዋና ፀሃፊ ዛፊር ስራኪያ የሃገራቸውን መሪ የረጂብ ጣይብ ኤርዶሃንን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ውስጥ ያሉ ሃሳቦችን በማድነቅ ንግግራቸውን የጀመሩት የተርኪዬው ሰው የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ዘመናትን የተሻገር ታሪካዊ ስለመሆኑ አስታውሰዋል፡፡
የረሽያው ገዢ ፓርቲ የዩናይትድ ረሺያ ፓርቲ ካውንስል አባል አንድሪ ኪሊሞቭ የፓርቲያቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የነበረ ወዳጅነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም የፓርቲው ተወካይ አረጋግጠዋል፡፡
ከአራት አመት በፊት ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበር ያስታወሱት ተወካዩ ብልፅግና ፓርቲ በትክክለኛ መንገድ እየተጓዘ መሆኑን ስለማረጋገጣቸውም ጮክ ባለ ድምፅ ሲናገሩ ተሰምተዋል፡፡
በካሳሁን አንዱዓለም