በተለይ የክልል ማዕከል በሆኑ ከተሞች እና በሌሎች የዞን ማዕከላት ተጠናክሮ እየተሠራ ይገኛል፡፡
ከፌዴራል፣ ከዞን፣ከከተማ አስተዳደር እና ከኅብረተሰብ ተሳትፎ በተገኝ ሀብት በስምንት ከተማ አስተዳደር ከተሞች እየተሠራ ይገኛል፡፡
ወላይታ ሶዶ፣ ዐርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ካራት እና ይርጋ ጨፌ ከተሞች በኮሪደር ልማት 41 ኪሜ መንገድ፣ 26 ሄክታር የአረንጓዴ ቦታዎችና የፓርክ ልማት፣ 9 የልጆች መጫወቻ ቦታዎች ፣11 ኪሜ የመንገድ ዳር መብራትና ሕንጻ የማስዋብ ሥራ እና 0.18 ሄክታር የአደባባይ ቦታዎች የማልማት ሥራ 3 ፋውንቴን ሥራዎይ ተሠርተዋል።
አንዳንዶች የመጀመሪያ ዙር አጠናቀው ሁለተኛ ዙር ጀምረዋል። አርባምንጭ ከተማ፣ የእግረኛ መንገድ 6ሜትር በአንድ በኩል፣ የብስክሌት መንገድ 3.2 ሜትር፣ አረንጓዴ ስፍራ 4ሜትር እና የመብራት Smart light ያካተተ ሥራ ተከናዉኗል።”
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት