AMN-የካቲት 4/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ለገቡ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች እንኳን ወደ ቤታችሁ በሰላም መጣችሁ ብለዋል፡፡
የጉባዔው ተሳታፊዎች ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የሰው ልጅ መገኛነት የሚያሳዩ ታሪኮችን፣ የተለያዩ ባህሎችን እና አስደናቂ መልክዓ ምድሮችን እንዲመለከቱም ጋብዘዋል፡፡
ከጉባዔው ባሻገር ከጥንታዊ ቅርስ ስፍራዎች እስከ ደማቅ ባህሎችና ወደር የለሽ የተፈጥሮ ውበትን ይመለከታሉ ሲሉም አስፍረዋል፡፡